የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የተቀናጀ የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ማእቀፍ

ግንቦት 17 ቀን 2014ዓ.ም
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የተቀናጀ የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ማእቀፍ (UN-GGIM: Integrated Geospatial Information Frame Work) ተግባራዊ ለማድረግ ብሔራዊ የድርጊት መርሀግብር (Country Action Plan –CAP) ሰነድ አዘጋጅቶ ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በካፒታል ሆቴል ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡ ውይይቱ ከግንቦት 17 – 18 ቀን2014ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
በወርክሾፑ የመክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ውይይቱም የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የብሔራዊ ስፓሻል ዳታ መሰረተ ልማት ማእከል ኃላፊ የሆኑት አቶ በሪሁ አለማየሁ የወርክሾፑን ዋና አላማ አስመልክተው ባደረጉት ገለፃ የተባበሩት መንግስታት አለማቀፍ የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን አስተዳደር (UN-GGIM) የተዘጋጀውን የተቀናጀ የጂኦስፓሻል የትግበራ እቅድ( Integrated Geospatial Information Frame Work) መሰረት በማድረግ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ሀገር አቀፍ የትግበራ እቅድ አዘጋጅቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያያት በፍጥነት ወደተግባር ለመግባት የዛሬው የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More