ተግባር እና ኃላፊነት

ኢንስቲትዩቱ በጂኦስፓሻል ሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂ እና ጂኦስፓሻል ዘርፍ የምርምርና የልማት ስራዎችን ከአገሪቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የትኩረት መስኮች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር በሀገር አቀፍ ደረጃ የጂኦስፓሻል መረጃ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የገጠርና ከተማ መሬት ምዝገባን ፣ የመሬት አጠቃቀም እቅድን ፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራን ፣ ግብርናን ፣ ከተማ ልማትን ፣ የውሃ ሃብት ጥበቃን ፣ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃን፣ የብዝሃ ህይወት ጥበቃ እና እንክብካቤ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ ለሕዝብ ቆጠራ፣ ለትራንስፖርት፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለካርታ ስራ፣ ለቅየሳ፣ ለሲቪልና ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ሰራዎች ለስማርት ከተማ አገለግሎት፣ ለአገር ደህንነት ወዘተ የሚደግፉ ከምድር፣ ከአየር ቅየሳ እና ከሳተላይት የሚገኙ ዳታ በመተንተን መረጃዎችንና ውጤቶችን የማቅረብ ሥራ ይሰራል፡፡ የጂኦስፓሻል መረጃዎችን ከማምረትና ከማሰራጨት ስራ በተጨማሪ፣ አገሪቱ የስፓሻል ኢንፎርሜሽን ለሃገር ልማት፣ መልካም አስተዳደር እና ደህንነት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ተጠቃሚ እንድትሆን ስፓሻል ዳታ መሰረተልማትን የማበልፀግና በአገር አቀፍ ደረጃ ስፓሻል ዳታ በአግባቡ ተደራሽ እንዲሆን የሚያስፈልጉ የህግና ፖሊሲ ጉዳዩችን፣ ስታንዳርዶችንና ስትራቴጂዎችን የማዘጋጀት ስራ ይሠራል፣ በአገሪቱ ውስት የሚመረቱ የጂኦስፓሻል ምርቶች ጥራትና ስታነዳርዳቸውን ይቆጣጠራል በተጨማሪም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ስልጣንና ተግባራት

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More