የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሰራተኞች በእንጦጦ ተራራ ላይ የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል በሚገኝበት 16 ሄክታር የሚሆን የማስፋፊያ መሬት ላይ የገብስ ዘር በመዝራት እና በአካባቢው ችግኝ በመትከል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን አራተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ ተቀላቀሉ::
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አብዲሳ ይልማ በእለቱ ባደረጉት ንግግር ይህ ስፍራ በቀጣይ ሀገራችን በስፔስ ዘርፍ ለምታከናውናቸው ፕሮጀክቶች ግንባታ እንዲውል ታስቦ የተዘጋጀ ነው:: በያዝነው የክረምት ወቅት መሬቱ ፆም እንዳያድር በማሰብ መንግስት በግብርና ምርት እራሳችንን ለመቻል ለያዘው እቅድ የራሳችንን አስትዋፅዖ ለማበርከት፣ የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የምርት መጠንን አስቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል መተግበሪያ ለመሞከር እና ሌሎችንም ተዛማጅ ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ፤ በ16 ሄክታር መሬት ላይ በዘሬው እለት የገብስ ዘር የተዘራ ሲሆን በአካባቢው የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች፣አመራሮች እና የክብር እንግዶች ከ2000 በላይ የሚሆኑ ችግኞችን በመትከል አርንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በእለቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ባይሳ በዳዳ በቦታው ተገኝተው የዘር መዝራት እና የችግኝ ተከላ ስነስርአቱን አስጀምረዋል፡፡
[masterslider id=”2″]