ዝርፊያና ውድመት ለተፈጸመበት ለኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ግማሽ ሚሊዬን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

ጅኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በትግራይ ወራሪ ቡድን ዝርፊያና ውድመት ለተፈጸመበት ለኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ግማሽ ሚሊዬን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ፡፡
መጋቢት 14/2014ዓ.ም ኮምቦልቻ ኮሚኒኬሽን፡፡
የጅኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ቱሉ በሻ /ዶክተር/ እንደገለጹት ተቋማችን ለኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ የመጀመሪያ ዙር ግማሽ ሚሊዬን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡ ድጋፉ ካለን ላይ ማህበራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ያደረገነው ነው ያሉት ዋና ዳሬክተሩ ኮሌጅን ለመደገፍ በቀጣይም ሁለቱ ተቋማት የጋራ ሁለትዮሽ የትብብር ተፈራርመው እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡ ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ኮሌጅን ሰራ ለማስጀመር የሚሆን ደስክ ቶፕ ኮምፒተሮች ,የእንግዳ ማረፊያ ወንበሮች ,የመሰብሰቢያ ጠረጴዛ ,ሸልፎች እና ሶፍዎች እንደሚገኙበት ዶክተር ቱሉ ገልጸዋል፡፡
በኮምቦልቻ በግብርና ኮሌጅ የአካዳሚክ ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ውቡ ታዬ በበኩላቸው ኮሌጅ በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር የነበረ ሲሆን በወራሪው ቡድን በደረሰበት ዝርፊያና ውድመት ከመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሏል ብለዋል፡፡ ተቋሙ በተለያዩ ተቋማት በሚደረግለት ድጋፍና በራሱ ጥረት ወደ ቀድሞው ሰራው በቅርቡ ይመለሳልም ብለዋል፡፡ ጅኦ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ያደረጉት ድጋፍ ስራ ለማስጀመር ወሳኝ ዕቃዎችን ናቸው ያሉት ምክትል ዲኑ ለተደረገልን ድጋፍ በኮሌጅ ሰም ምስጋና አቅርበዋል፡ ፡

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More