የዑጋንዳ ፓርላማ አባላት ልዑካን በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ዘርፎች ልምድ ልውውጥ አደረጉ

የዑጋንዳ ፓርላማ አባላት ልዑካን በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ዘርፎች ልምድ ልውውጥ አደረጉ ፦
==============
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የዑጋንዳ ፓርላማ አባላት ልዑካን ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡
የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ እና የዘርፉ ተመራማሪዎች ስለ ኢንስቲትዩት ትሩፋቶች እና እየተከናወኑ ባሉ የዘርፉ ክንውኖችን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከየዑጋንዳ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በዘርፉ በትብብር ሊሰሩባቸዉ በሚችሉ መስኮች ላይ ውይይት እና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
የየዑጋንዳ ፓርላማ አባላት ልዑካን በእንጦጦ ኦቭዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን ዘርፉን ለመደገፍ የሚያግዙ መሠረተ ልማቶችን ለማጠናከር የሚያስችሉ ክንውኖች በመመልከት ሀገራቸው በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
ትብብሩን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያላቸውን ጥረት ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተው በትብብር የሀገራቸው መንግስት እንደሚሰራ የዑጋንዳ ፓርላማ አባላት ልዑካን ተናግረዋል፡፡
የዑጋንዳ ፓርላማ የልዑካን ቡድን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፎች ከኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
ልዑካኑ በቆይታቸው የሳይንስ ሙዚየምን፣ የአዕምሯዊ ንብረት እና የቴክኖሎጂ ባለስልጣንን የሚጎበኙ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በአቀባበል ስነስርዓት ላይ ገልፀዋል።

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More